አቶ ሚልዮን ቴጂ

አቶ ሚልዮን ቴጂ በአዲስ አበባ ከተማ፤ ጉላሌ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 09 ነዋሪ ሲሆኑ ዕድሜያቸው 38 ዓመት እና የዲግሪ ምሩቅ ናቸው፡፡ አቶ ሚልዮን የደቦ ማይክሮፋይናንስ ደንበኛ ከመሆናቸው በፊት ምንም የገቢ ምንጭ አልነበራቸውም፡፡
አቶ ሚልዮን የደቦ ማይክሮፋይናንስ ደንበኛ ከሆኑ በኃላ በንብረት ዋስትና የብድር አገልግሎት በማግኘት በኮንስትራክሽን ስራ ላይ ተሰማርተው የገቢ ምንጭ ፈጥሯል፡፡ በተለያዩ የብድር ዙሮች ባገኙት ብድርና የምክር አገልግሎቶች የተሰማሩበትን ስራ በማስፋፋትና ገቢያቸውን በማሳደግ ዓለማቸውን ያሳኩ ሲሆን በተጨማሪም ለሌሎች ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ችለዋል፡፡
“ከደቦ ማይክሮፋይናንስ ባገኘሁት ፈጣን የብድር አገልግሎት ዓላማዬን ማሳካት ችያለሁ፡፡ የገቢ ምንጬ ከማደጉ የተነሳ የራሴ የሆኔ የብሎኬት ማምረቻ ማሺንና የስራ መኪናዎችን መግዛት ችያለሁ፡፡ እንዲሁም የባለ ሁለት መኝታ ኮንዶሚኒዬም ክፍያ በመክፈል የቤት ባለቤት ሆኛለሁ፡፡ በተጨማሪም ለ 7 ወጣቶች የስራ እድል መክፈት ችያለሁ፡፡ ከደቦ ማይክሮፋይናንስ ያገኘሁት ትልቅ ጥቅም ከትንሽ ንግድ ተነስቶ ማደግ እንደሚቻል የተገነዘብኩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የትልቅ ንግድ ስራ ባለቤት እንደሆንኩ ይሰማኛል፡፡ በመሆኑም አሁን የደረስኩበት ደረጃ ላይ ለመድረስ የማይክሮፋይናንሱ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበረ፡፡”

