የደንበኞች የስኬት ታሪክ እና ምስክርነት

  • አቶ አብዲሳ ቀሹ :-
አቶ አብዲሳ ቀሹ በስራ ቦታ

አቶ አብዲሳ ቀሹ በኦሮሚያ ክልል ዱግዳ ወረዳ መቂ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ዕድሜያቸው 31 ዓመት እና የዲግሪ ምሩቅ ወጣት ናቸው፡፡ አቶ አብዲሳ የደቦ ማይክሮፋይናንስ ደንበኛ ከመሆናቸው በፊት ስራ አጥና ምንም የገቢ ምንጭ ያልነበራቸዉ ግለሰብ ነበሩ፡፡

አቶ አብዲሳ የደቦ ማይክሮፋይናንስ ደንበኛ ከሆኑ በኃላ በቤት ዋስትና የብድር አገልግሎት በማግኘት በዶሮ እርባታ ስራ ላይ በመሰማራት የገቢ ምንጭ መፍጠር የቻሉ ሲሆን በተለያዩ የብድር ዙሮች ባገኙት የብድር አገልግሎት የተሰማሩበትን ስራ ከማስፋፋትም በላይ ተጨማሪ የቡቲክ ንግድ በመክፈት ገቢያቸውን በማሳደግ አሁን ላይ የመኖሪያ ቤታቸዉን እየገነቡ ይገኛሉ፡፡

“ከደቦ ማይክሮፋይናንስ ባገኘሁት ብድር የዶሮ እርባታ ስራ በመጨመር በጊዜ ሂደት ገቢዬ በመጨመሩ ተጨማሪ የቢቲክ ንግድ ስራ ከፍቻለሁ፡፡ እያገኘሁትም ባለዉ ገቢ የመኖሪያ ቤቴን እየገነባሁ እገኛለሁ፡፡ የቁጠባን ባሕልም ያዳበርኩ ስሆን ባገኘሁትም የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በጣም ረክቻለሁ፡፡” 

አቶ አብዲሳ ቀሹ በስራ ቦታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *