ብድር እንዴት ያገኛሉ? የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዴት መሆን ይችላሉ? ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አገልግሎቱን ለማስፋትና የደንበኞቹን ፍላጐትና እርካታ ለማሟላት ሲባል ሁለት ዋና ዋና የብድር አሰጣጥ ዘዴዎችን በመጠቀም የተቀላጠፈ የብድር አገልግሎት እያቀረበ ይገኛል፡፡ በቡድን በአንድ አካባቢ የሚገኙ እንዲሁም ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር ያላቸው በጥቃቅን ንግድ ና ግብርና ስራዎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ከሦስት እስከ አምስት በሚሆን የቡድን አባል በመደራጀት የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡ በግል የግል ብድር ተጠቃሚ ደንበኞች በአንጻራዊነት የተሻለ የብድር መጠን የሚያገኙ ሲሆን በቂ የብድር ዋሰትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለእርሰዎ በሚቀርብዎት አድራሻ በመገኘት የአገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ !!! አድራሻዎቻችን