የፍቃደኝነት ቁጠባ ማለት ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል ወይም የተቋሙ ደንበኛ የሆኑ ግለሰቦች የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን በራሳቸው ፍላጎት የሚቆጥቡት የቁጠባ አይነት ነው፡፡ የፍቃደኛ ቆጣቢ ደንበኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የቆጠቡትን ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፡፡

የፍቃደኝነት ቁጠባ በሦስት የቁጠባ ዓይነቶች ይመደባሉ፡፡

ተበዳሪ ለሆኑ መደበኛ የፍቃደኝነት ቁጠባ

የተቋሙ የብድር ተጠቃሚዎች በፍላጐታቸው የሚያስቀምጡት መደበኛ የቁጠባ ዓይነት ሲሆን የቁጠባ ባህልን ለማሳደግና ቁጠባን ለማበረታታት ታስቦ የተዘጋጀ የቁጠባ ዓይነት ነው፡፡

ተበዳሪ ላልሆኑ የፍቃደኛነት ቁጠባ

የተቋሙ የብድር ተጠቃሚ ያለሆኑ ግለሰቦች ወይም የህብረተሰብ ክፍሎች  የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን በፍላጐት የሚያስቀምጡትና ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ወጪ አድርገው የሚጠቀሙበት የቁጠባ ዓይነት ነው፡፡

የጊዜ ገደብ ተቀማጭ

የተሻለ የቁጠባ ወለድ የሚያስገኝ ሆኖ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ወጪ የማይደረግ ወይም በጊዜ የሚወሰንና በፍላጎት ላይ የሚመሰረት የቁጠባ ዓይነት ነው፡፡

ደንበኞች ቁጠባቸውን  ወጪ ማድረግ  ሲፈልጉ በተቋሙና ባስቀማጭ የውል ስምምነት መሰረት ቀድመው ለተቋሙ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡