ከቡድን የብድር አገልግሎት ጋር የሚያያዝ የቁጠባ ዘርፍ ሲሆን ደንበኞች ለሚበደሩት ብድር ዋስርና እንዲሆን እንዲሁም የቁጠባ ባህል እንዲዳብርና ቁጠባን ለማበረታታት የቀረበ የቁጠባ አይነት ነው፡፡

ቅድመ ብድር ቁጠባ

የቡድን ብድር ተጠቃሚዎች ብድር ከመውሰዳቸው በፊት የሚቆጥቡ የቅድመ ብድር የግዴታ ቁጠባ ዓይነት ነው፡፡ ይህ የቁጠባ ዓይነት ደንበኞች ብቁ ከሚያደርጉ ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ነው፡፡

መደበነኛ የግዴታ ቁጠባ

ማንኛውም የቡድን ብድር ተጠቃሚ ደንበኞች ከወርዊ የብድር ተመላሽ ክፍያዎች ጋር ማድረግ ያለማቋረጥ የሚቆጥቡ መደበኛ ቁጠባ ነው፡፡ ብድሩ ሙሉበሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቋሚነት ተቀማጭ የሚደረግ ሲሆን ሁሉም አባላት ዕዳቸው እስቀሚጠናቀቅ ድረስ ወጪ የማይደረግ የቁጠባ ዓይነት ነው፡፡