ስለእኛ

ልዩ የሚያደርጉን

ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች በመጠቀም የተቀላጠፈ አገልግሎት በማቅረባችን

ፈጣንና ጊዜውን የጠበቀ አገልግሎት እየሰጠን በመሆናችን

ልዩ ልዩ የብድር እና የቁጠባ አገለግሎቶችን የሚናቀርብ በመሆናችን

የደንበኞቻችን እርካታ በትልቁ ለማሟላት በታታሪነት የሚንሰራ በመሆናችን

ራዕይ

አዳዲስ ቀልጣፋ እና ዘላቂ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ በሀገሪቱ ቀዳሚ የማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን መሆን::

ተልእኮ

  • ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ግለሰቦች እንዲሁም ተቋማት አዳዲስና ዘላቂ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ ደንበኞች በንግድ ስራና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የላቀ እርካታ እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡

ዓላማ

ደንበኞችና አጠቃላይ ህብረተሰብ ገንዘቡን ትርፋማ የንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞች መልሶ በማበደር ደንበኞቹ በንግድ ስራና በኢኮኖሚ ደረጃ መሻሻል እንዲያሳዩ ማድረግ አጠቃላይ ዓላማው ሲሆን ዋና ዋና ዝርዝር ዓላማዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • የውዴታና ግዴታ ቁጠባ እንዲሁም የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ከደንበኞችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሰብሰብ፤
  • ለብድር ብቁ ለሆኑ ነጋዴዎች፤ ግለሰቦች፤ የግብርና ስራ ላይ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም ለተለያዩ ተቋማት የብድር አገልግሎት ማቅረብ፤
  • አነስተኛ የማይክሮ ክሬዲት ኢንሹራንስ አገልግሎቶችን መስጠት፤
  • ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ የግምጃ ቤት ሰነዶችንና ሌሎች የአጭር ጌዜ የንግድ ወረቀቶች በኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት መግዛት፤

 

  • ሥራውን የሚያከናውንባቸውን ሕንፃዎች ጨምሮ ማናቸውንም የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ  ንብረት በባለቤትነት መያዝ፣ መንከባከብና ለሌሎች ማስተላለፍ፤
  • ለደንበኞች የአመራር፤ የገበያ፤ የቴክኒክና አስተዳደራዊ ምክር በመስጠት ደንበኞች የሚያካሄዷቸውን ገቢ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶች ማገዝ፤
  • በሊዝ አዋጅ ቁጥር 103/1998 መሰረት ብቁ ለሆኑ ደንበኞች የሊዝ አገልግሎት መስጠት፤
  • ገንዘብ የማስተዳደር እና የሀገር ውስጥ ሐዋላ አገልግሎቶችን መስጠት ናቸው፡፡