የጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ብድር

የጥቃቅን ንግዶችና አገልግሎቶች፤ ማኑፋክቸሪንግና ፕሮሰሲንግ ወዘተ ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች የሚሰጥ የብድር ዓይነት ሲሆን ንግድ ፍቃድ ኖሯቸው ወይም ሳይኖራቸው  እድገት ተኮር ስራዎች ላይ የተሰማሩ የተለያዩ  የህብረተሰብ ክፍሎች በግል የማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ብድር ተጠቃሚ የሚሆኑበት የብድር አይነት ነው፡፡

የአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ብድር

የአነስተኛ ንግዶችና አገልግሎቶች፤ ማኑፋክቸሪንግና ፕሮሰሲንግ ወዘተ ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች የሚሰጥ የብድር ዓይነት ሲሆን ንግድ ፍቃድ ኖሯቸው  እድገት ተኮር ስራዎች ላይ የተሰማሩ የተለያዩ  የህብረተሰብ ክፍሎች በግል የአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ብድር ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

የሀውስሆልድ ብድር

የቤት ውስጥ ዕቃዎችን ለምሳሌ ፈርኒቸሮችን፤የማብሰያ ዕቃዎችን፤ የልብስ እጥበት ማሽኞችን ፍሪጆችንና የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን ለምሳሌ እንደ ሶላር ሲስተም ባዮጋዝ ያሉትን ገዝተው መጠቀም ለሚፈልጉ እንዲሁም የኮንደሚኒየም ዕጣ ዕድል ደርሷቸው ቅደወመ ክፍያ ለመክፈል ብድር ለሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጥ የብድር አገልግሎት ነው፡፡

የሰራተኛ ብድር

መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆነ እንዲሁም የግል መስሪያ ቤት በቋሚነት ተቀጥረው ለሚሰሩ ሰራተኞች የሚሰጥ ሲሆን ለትምህርት ቤት ክፍያ፤ የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ፤ ለህክምና፤ ለሰርግ ወዘተ ወጪዎች መሸፈኛ የሚሆን የብድር አገልግሎት ነው፡፡

ልዩ ብድር

ለግለሰብ ወይም ለድርጅት የሚሰጥ ብድር ሲሆን ለስራ ማስኬጃ፤ የባለቤትነት ስም ማዘዋወሪያ፤ ለደሞዝ ክፍያ፤ ለገቢዎችና ግምሩክ ባለሥልጣን፤ ለቢሮ ክራይ ክፍያ፤ ለህክምና ወጪዎች፤ ለእንሹራንስ ክፍያ ገንዘብና ለተለያዩ የአጭር ጊዜ ወጪዎች መሸፈኛ የሚውል እስከ ስድስት ወር ጊዜ ብቻ የሚቆይ የልዩ ብድር አገልግሎት ነው፡፡

 

አሻጋሪ ብድር

ለቋሚ ተቀጣሪ ሰራተኞች የተዘጋጀ ብድር ሲሆን ደሞዝ ተቀብለው ከአስር ቀን ቆይታ በኃላ የሚገጥማቸውን ድንገተኛ የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ የታሰበና ከአስር እሰከ ሃያ ቀናት ብቻ የሚቆይ በጣም የአጭር ጊዜ የብድር አግልግሎት ነው፡፡

 

ታዳሽ ወይም በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የሶላር ዕቃዎች መግዣ ብድር

ታዳሽ ወይም በፀሓይ ኃይል የሚሰራ የሶላር ዕቃዎችና ሶላር  በአጭርና መካከለኛ ጊዜ ብድር ገዝተው ለመጠቀም ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች የተዘጋጀ የብድር ዓይነት ነው፡፡